Thursday, October 17, 2013

አያገባህም አትበሉኝ!

                                  

ኢትዮጵያ የእኔም የናንተም የሁላችንም ሀገር ነች::የእኔም ሀገር በመሆኑዋ የእሱዋ ጉዳይ እንደናንተ ሁሉ ያገባኛል:: የማይሆን ነገር ሊሆን አይችልምና በከንቱ አትድከሙ:: የኢትዮጵያዊነት ስሜቴን እንኩዋን እናንተ ምንም ሀይል ሊሸረሽረዉ አይችልም:: እትብቴ ተቀብሮባታልና እኛ በቀየስንልህ ቦይ ብቻ ፍሰስ አትበሉኝ ለሀገሬ የሚጠቅማትንና የሚጎዳትን ለይቸ አዉቃለሁ:: ያልሆንኩትን ስም በመለጠፍ የሀገሬ ጠላት አታስመስሉኝ:: ደማችን ቢመረመር ማን ጥልቅ የኢትዮጵያዊነት ፍቅር እንዳለዉ ይታወቃል ዳሩ ምን ያደርጋል "ፍየል ከመድረሱዋ ቅጠል መበጠሱዋ " ሆነና ነገሩ ትናንት ኢትዮጵያዊነት ፈፅሞ በዉስጣችሁ ያልነበረ ...ዛሬ ከኛ በላይ ለኢትዮጵያ ተቆርቁዋሪ የለም ትሉኛላችሁ:::: ቦርቄ ያደኩበትን ሜዳም(አደባባይ) አትከልክሉኝ እናንተ ሳትመጡ ጀምሬ ተንከባክቤ አቆይቸዋለሁና:: ማን ጠብቆ ያቆየዉን አደባባይ ማን ያዝዝበታል? የምሄድበትን መንገድም ሆነ የምለብሰዉን ልብስ ከቶ አትመርጡልኝም ባህሌን ጠብቄ የመሄድ ግዴታ አለብኝና:: ከነማን ጋር መዋል እንዳለብኝም አትንገሩኝ እናንተ ስለመጣችሁ ወዳጆቼን ልከዳቸዉ አልችልም:: ባጠቃላይ ስለ ሀገሬ አያገባህም አትበሉኝ ከናንተ የበለጠ የሀገር ፍቅር አለብኝና:: ለሁሉም ነገር ጊዜ ፍርድ እስከሚሰጥ በሚከተለዉ የዘፈን ስንኝ ልለያችሁ

"ጊዜ የሙዝ ልጣጭ ሆኖ አዳልጦሽ
ወድቀሽ እንዳላይሽ ተራምደዉ ሲያልፉሽ"

No comments:

Post a Comment